ዜናዎች

ስለእኛ

አቶ ወሊድ አንዋር ሀሊፋ

በአሶሳ ከተማ አስተዳደር የወረዳ ሁለት ን/ኢን/ትራ/ጽ/ቤት ሀላፊ

የሀላፊው መልዕክት   

የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ወረዳ ሁለት ንግድ ኢንድስትሪ ትራንስፖርት ጽ/ቤት መንግስት ባለፈዉ ስትራቴጂክ ዘመን ያሉበትን ሰፊ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ ተከታታይ የሆነ ጥረት ማድረጉና አበረታች ዉጤቶችን ማስመዝገቡ ይታወቃል፡ ለውጤቶቹ መገኘት ከፍተኛዉን አስተዋጽኦ ያደረጉት ባለፉት አምስት ተከታታይ ዓመታት ዉጤታማነታቸውን በተግባር ያረጋገጡት ሀገራዊ የልማትና የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ሲሆኑ በሃገር አቀፍ ደረጃ የተያዘው የረዥም ዘመን ጠቋሚ የልማት እቅድ ላይ በመመርኮዝና ትኩረት የተሰጠባቸውን አቅጣጫዎች በመከተል በከተማችን ተፈፃሚ ለማድረግ የተደረገ ጥረት እና ከክልል ንግድ የሚወርድልንለይተን ስትራተጂያዊ ዕቅድ በማዘጋጀት ሰፊ እንቅስቃሴ በማድረጋችን የከተማውን መልካም አስተዳደር ችግሮች ለማስፈን ፤ሰላም እንዲሰፍንና  የህዝቦች ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በየደረጃዉ ያለዉ መዋቅራችን ርብርብ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡በዚሁ መሰረት የለውጥ መሳሪያዎችን ተግባራዊ በማድረግ ጥራት ያለውና ፈጣን አገልግሎት በማረጋገጥ ደንበኞችን በማርካት ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ የተለያዩ ተግባራት በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ የተጀመረውንም የለውጥ ሂደት ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ እንዲቻል የዘመኑ ቴክኖሎጂ ባፈራው ስትራቴጂያዊ የስራ አፈፃፀም አመራርና ምዘና ስርዓት መጠቀም የግድ የሚል በመሆኑ ስትራቴጂያዊ የስራ አመራርና ውጤት ተኮር ምዘና ስርዓት ጥናት ማካሄድና ወደ ተግባር መሸጋገር አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ይህን እድገት ቀጣይነት እንዲኖረው ለማድረግ ሀገራዊ የዕድገትና የትንራስፎርሜሽን ዕቅድ ተዘጋጅቶ ሰፊ እንቅስቃሴ እየተደረገ ሲሆን መምሪያችን የመንግስትን የልማት እቅድና የትኩረት አቅጣጫ ባገናዘበ መልኩ በአዲሱ የዉጤት ተኮር ስርዓት የተቃኘ ሊተገበር የሚችል የቀጣይ 2015(1/2) እስከ 2017 ዓ.ም የተከለሰ ስትራቴጂክ፤የልማት፣ዕቅድ ለማዘጋጀት ተችሏል፡፡