.የአሶሳ ከተማ አስ/ረ የወረዳ ሁለት ን/ኢ/ት ጽ/ቤት ሥልጣንና ተግባራት፡-
- ንግድ፣ እንዲስፋፋ የተመቻቹ ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ ያደርጋል፤
- የወረዳችን ንግድን ለማስፋፋትና ለማጠናከር ቀልጣፋ የግብይት ሥርዓትና ተገቢ የንግድ አሠራር እንዲሰፍን ያደርጋል፤
- አግባብ ባለዉ ሕግ መሠረት የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት ይሰጣል፣ ፣ ይሰርዛል፣ የንግድ መዝገብ ያደራጃል፤
- ተገቢ ያልሆኑ የንግድ አሠራር ለመከላከል የሚያስችል የተሟላ ሥርዓት ይዘረጋል፣የንግድ ህጎች መከበራቸዉን ያረጋግጣል፣ አፈፃፀማቸዉን ይከታተላል፤
- በህጉ መሠረት ለሸማቾች ጥበቃ ያደርጋል፣ የንግድ ዕቃዎችንና ሥርጭት ይቆጣጠራል፤
- በወረዳችን የዋጋ ተመን ላይ ክትትልና ቁጥጥር ያደርጋል፤
- የወረዳችን ህጋዊ ሥነ-ልክ ሥርዓት በአግባቡ መተግበሩን ክትትልና ቁጥጥር ያደርጋል
- በወረዳችን የትራንስፖርት ህጎች እንዲከበሩ ክትትልና ቁጥጥር ያደርጋል
- በወረዳችን የታሪፍና የፌርማታ ቁጥጥርና ክትትል ያደርጋል
- በወረዳዉ የመንገድ ትራንስፖርት ህጎች መከበራቸዉን ይከታተላል፣ እርምጃ ይወስዳል፤
- አሽከርካሪ ተሸከርካሪዎችን ይቆጣጠራል አስፈላጊውን እርምጃ ይወሰዳል
- በማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች እንዲስፋፉ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር ድጋፍና ክትትል ያደርጋል
- ከከተማ እናሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር የመንገድ ትራፊክ አደጋ ለመከላከል በቅንጅት ይሰራል፣ በወረዳችን የመንገድ ትራንስፖርት እንዲሳለጥ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል
- ዓላማዉን ለማስፈፀም የሚችሉ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ያከናዉናል፡