ዜናዎች

የማብራት ሀይል መቋረጥ ምክንያት በማደረግ በምርቶች ላይ ዋጋ የሚጨመሩ ነጋዴዎች ከድረጊቱ እራሳችው እንዲቆጠቡ የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ አቶ አስር ኢብራሂም አሳሰቡ ።

ሀምሌ 03/2016 ዓ.ም የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ሀላፉ አቶ አስር ኢብራሂም በወቅታዊ የዋጋ ንረት ዙሪያ ከአሶሳ ከተማ አስተዳደር ከጥራጥሬ እና የዛይት አቅራቢ ነጋዴዎች ጋር ወይይት አካሄደዋል ።

በእህልና ዘይት ንግድ ስራዎች ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎችን በመሰብሰብ ከወቅቱ የመብራት መጥፋት ጋር ተያይዞ በመሰረታዊ የምግብ ፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ እየተስተዋለ ስለሚገኝ ይህንን ለማረጋጋት ከአከፍፍዮችና ቸርቻሪዎች ጋር ውይይት ተካሂዷል

በከተማው ላይ ለሁለት ሳምንት የተቋረጠው የማብራት ሀይል ምክንያት በመደረግ በምርቶች ላይ ነጋዴዎች ዋጋ በመጨመራቸው ከዚህ ድርጊት እራሳችው እንዲቆጠቡ ለነጋዴ ማህበረሰቡ የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ አስር ኢብራሂም አስገንዝቧል ።

የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ንግድና ኢንዱስትሪ መምሪያ አቶ አቡጣልፍ እንደገለፁት በአሁን ሰዓት ህዝብ ከመበዝበዝ ይልቅ ህዝብን በአግባቡ ማገልገል ከነጋዴ ማህበረሰብ እንደሚጠበቅ ገልጿው ህዝብ በአግባቡ የሚያገለግሉ ነጋዴዎች እውቅና በማስጣት ነገር ግን ዋጋን በመጨመር ማህበረሰቡን ላልተገባ የኑሮ የሚዳረጉ ነጋዴዎች ላይ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድ ተነግሯል ።

በሚከሰቱ ክስቴቶች አጋጣሚን ተጠቅሞ ዋጋ በሚጨምሩ ነጋዴዎቹ ላይ የንግድ በህጉ መሠረተ በመደረግ ጽ/ቤቱ እርምጃ በሚገባ በልማውሰዱ ማህበረሰቡ ላልተገባ የኑሮ ውድነት እየተደረገ በመሆኑ ከውይይቱ በመነሳት ግን የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድ የወረዳ ሁለት ንግድና ትራንስፖርት ጽ/ቤት ሀላፉ አቶ ወዋሊድ አንዋንር ተነገሯል።

የውይይቱ ተሳታፊዎችም የንግድ ዘርፍ ጥብቅና ክትትል ማነስ ነጋዴዎች ያልተሰማሩበት የንግድ ዘርፍ ላይ በመሰማራታቸው የንግዱ ሥራዓቱን በመቀላቀል እየተበላሸ ያለው የንግድ ሥርዓቱ መስተካከል እንሚገባም ጠቁሟል ።

የንግድ ተቋሙ መውሰድ ያለበት ክፍቴቶችእንዲሁም ነጋዴውም መውሰድ ያለባቸው ክፍቴቶች ወስዶ መስተካከል እንደለበት አቶ አስር ኢብረሂም ገልጾው ከለአግባብ ዋጋን የሚጨምሩ እና ዘርፍ በመቀላቀል የሚቀሰቀሱ ነጋዴዎች የንግድ ህጉ ተከትሎ እርምጃ ለመውሰድ ተቋሙ የሚገደድ መሆኑን አሳስበዋል ።

የከተማው ነጋዴዎች ህብረተሰቡ አሁን ከለበት ችግር ለማውጣት በአግባቡ ማግለገል እንደለበት እና ዋጋ በልማጨመር ህበረተሳቡን ማገልገል እንደለበት አቶ አስር በአጽኖት አሳስበዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *