ዜናዎች

የ2017 በጀት አመት የንግድ ፈቃድ እድሳት ሀምሌ 1 ቀን እንደሚጀመር የወረዳ ሁለት ንግድ እንዱስትሪ ትራንስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ወሊድ አንዋር ገለጹ ።

(ሰኔ 30/2016 ዓ.ም) በአሶሳ ከተማ አስተዳደር ወረዳ ሁለት ነጋዴ ማህበረሰቦች እንደሚታወቀው የንግድ ሥራ ፍቃድ በየበጀት ዓመቱ ከሐምሌ 01 ቀን እስከ ታህሳስ 30 ቀን ባሉት 6 ወራት ውስጥ መታደስ አንዳለበት የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 980/2008 ዓ.ም ይደነግጋል። ስለሆነም በተጠቀሰው የፍቃድ ማሳደሻ ጊዜ ውስጥ ፈቃዳቸው ያለሳደሱ የወረዳው ነጋዴዎች በአዋጅ ቁጥር 980/2008 ዓ.ም መሠረት ከጥር 01ቀን እስከ…

Read More

የንግዱ ማህበረሰብ ግዴታውንና መብቱን ተረድቶ እንዲሰራ የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት አሳሰበ፡፡ ምክር ቤቱ በባለፈው በጀት ዓመት አፈፃፀም ሪፖርትና በ2017 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር መክሯል፡፡

የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አብዱከሪም አብዱራሂም እንዳሉት የንግዱ ማህበረሰብ ለሀገር ዕድገት የሚያበረክቱት አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው ግብርን በታማኝነት መክፈልንም ባህል እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡ የንግዱ ማህበረሰብ በበጎ አድራጎት ስራዎች፣ በከተማ ፅዳትና ውበት፣ የዋጋ ንረትን በመቅረፍና በመሰል ስራዎች ግንባር ቀደም ተሳታፊ እንዲሆኑም ከንቲባው ጥሪውን አቅርበዋል፡፡ የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ደሳለኝ በንቲ በበኩላቸው…

Read More