ዜናዎች

የንግዱ ማህበረሰብ ግዴታውንና መብቱን ተረድቶ እንዲሰራ የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት አሳሰበ፡፡ ምክር ቤቱ በባለፈው በጀት ዓመት አፈፃፀም ሪፖርትና በ2017 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር መክሯል፡፡

የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አብዱከሪም አብዱራሂም እንዳሉት የንግዱ ማህበረሰብ ለሀገር ዕድገት የሚያበረክቱት አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው ግብርን በታማኝነት መክፈልንም ባህል እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡

የንግዱ ማህበረሰብ በበጎ አድራጎት ስራዎች፣ በከተማ ፅዳትና ውበት፣ የዋጋ ንረትን በመቅረፍና በመሰል ስራዎች ግንባር ቀደም ተሳታፊ እንዲሆኑም ከንቲባው ጥሪውን አቅርበዋል፡፡

የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ደሳለኝ በንቲ በበኩላቸው የንግዱ ማህበረሰብ ግዴታውንና መብቱን ተረድቶ እንዲሰራ ምክር ቤቱ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በከተማው ከ1ሺህ በላይ የምክር ቤት አባላት መኖራቸውን የጠቀሱት ፕሬዚዳንቱ በቀጣይም በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮች እንዲታረሙ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ንግድ መምሪያ ኃላፊ አቶ አቡጣሊብ አላሚር እንዳሉት ደግሞ እንደሀገር መተግበር የተጀመረውን የማይክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም በከተማዋ የዋጋ ንረት እንዲፈጠር የሚሰሩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስበዋል፡፡

የከተማው ንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት አባላት በሰጡት አስተያዬት በበጀት ዓመቱ ም/ቤቱ በግንዛቤ ፈጠራና ህገ-ወጥ ደረሰኝን ለመከላከል አበረታች ስራዎች ማከናወኑን ጠቁመው ሆኖም አላስፈላጊ የኬላ ቀረጥ እንዲቆምና በዘርፉ የሚስተዋሉ መሰል ክፍተቶች እንዲታረሙም ጠይቀዋል፡፡

ባለፈው በጀት ዓመት ለከተማው ንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት አፈጻጸም ጉልህ ሚና ለነበራቸው አካላት የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡

በአሶሳ ከተማ አስተዳደር የወረዳ ሁለት መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *