ዜናዎች

የ2017 በጀት አመት የንግድ ፈቃድ እድሳት ሀምሌ 1 ቀን እንደሚጀመር የወረዳ ሁለት ንግድ እንዱስትሪ ትራንስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ወሊድ አንዋር ገለጹ ።

(ሰኔ 30/2016 ዓ.ም) በአሶሳ ከተማ አስተዳደር ወረዳ ሁለት ነጋዴ ማህበረሰቦች እንደሚታወቀው የንግድ ሥራ ፍቃድ በየበጀት ዓመቱ ከሐምሌ 01 ቀን እስከ ታህሳስ 30 ቀን ባሉት 6 ወራት ውስጥ መታደስ አንዳለበት የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 980/2008 ዓ.ም ይደነግጋል።

ስለሆነም በተጠቀሰው የፍቃድ ማሳደሻ ጊዜ ውስጥ ፈቃዳቸው ያለሳደሱ የወረዳው ነጋዴዎች በአዋጅ ቁጥር 980/2008 ዓ.ም መሠረት ከጥር 01ቀን እስከ ሰኔ 30 ቀን ላለው ጊዜ ከፍቃድ ማሳደሻው በተጨማሪ ፈቃድ ማሳደሱ ለዘገየበት ለጥር ወር ብር 2500 (ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር) እና ለሚቀጥለው እያንዳንዱ ወር ብር 1500 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር) ቅጣት በመክፈል ፈቃዱን ያሳድሳል።

በመጨረሻም የ2017 በጀት ዓመት የንግድ ፈቃድ እድሳት ሀምሌ 1ቀን እንደሚጀምር ለንግዱ ማህበረሰብ አገልግሎቱን ከብልሹ አሰራር በጸዳ ደረጃ በተሻለ ቅልጥፍ ለመስጠት በቂ ዝግጅት መድረጉ የወረዳ ሁለት ንግድ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ወሊድ አንዋር አስታወቀ ።

ህገወጥ ንግድን በጋራ እንከላከል

በአሶሳ ከተማ አስተዳደር የወረዳ ሁለት ንግድ ኢንደስትሪ ትራንስፖርት ጽ/ቤት

በአሶሳ ከተማ አስተዳደር የወረዳ ሁለት መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

One thought on “የ2017 በጀት አመት የንግድ ፈቃድ እድሳት ሀምሌ 1 ቀን እንደሚጀመር የወረዳ ሁለት ንግድ እንዱስትሪ ትራንስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ወሊድ አንዋር ገለጹ ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *