ነሐሴ 07/2016 የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ወረዳ ሁለት ንግድ ጽ/ቤት፤
የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ወረዳ ሁለት ንግድ ጽ/ቤት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ተግባራዊ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ በወረዳው የተቋቋመው የንግድ ቁጥጥር የጋራ ግብረሃይል 1052 የንግድ ተቋማት ላይ የተደረገው ክትትል ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ ያደረጉና ምርት በማከማቸት በድምሩ 45 የንግድ ድርጅቶችን በማሸግ 3 ታስረው እንዲጠየቁ መደረጉን ኃላፊው ገልፃዋል።
ያልተገባ የዋጋ ጭማሪና የምርት ክምችት የሚያደርጉ ስግብግብ ነጋዴዎች ላይ እየተወሰደ ተጠናክሮ የሚቀጥል በመሆኑ ህብረተሰቡ ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ ሲያጋጥመው አቅራቢያው ላለው የንግድ ተቋም ጥቆማ በመስጠት እንዲሁም የግብረሀይል ተቆጣጣሪዎች የስልክ መስመር +251917709817/ +251 91 340 4416 ደውሎ ጥቆማ በመስጠት ሕገ-ወጥ ንግድ እንዲከላከል የጽ/ቤቱ ኃላፊ አሳስበዋል ፡፡
ዘገባው የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ወረዳ ሁለት ንግድ ጽ/ቤት


