(አሶሳ ፣ ህዳር 13 ፣ 2017) በአሶሳ ከተማ አስተዳደር የወረዳ ሁለት ንግድ ጽ/ቤት የተለያዩ የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸውን የፋብሪካ ምርቶችን የመሰብሰብና የንግድ ፈቃድ በሌላቸው የንግድ ቤቶች ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለፀ።።
ጽ/ቤቱ የተለያዩ የተጭበረበሩ ሚዛኖችን ድንገተኛ ፍታሻ በማድረግ እርምጃ እንደወሰደ ተመልክቷል።
የወረዳ ሁለት ንግድ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ወሊድ አንዋር እንደገለፁት ተቋሙ ድንገተኛ የሚዛን ምርመራን ጨምሮ ያለ ንግድ ፈቃድ የሚሰሩ ነጋዴዎች የመለየት ሥራ እና መጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸውን ምርቶች የመሰብሰብ ተግባር ላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህ መነሻ በርካታ የንግድ ሱቆች ላይ መጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው ምርቶች ስለመኖራቸው የገለፁት ኃላፊዉ በተቋሙ ለዚሁ አላማ በተሰማሩ አካላት ተይዞ እርምጃ መውሰዱን ገልጸዋል።
በመጨራሻም ወቅቱን ምክንያት በማድረግ የተለየዩ ምርቶች ላይ ዋጋ በሚጨምሩ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ እየተወሰደ እንዳሆነ የገለፁት ኃላፊዉ ከላይ በተዘረዘሩት በሁሉም ዘርፎች ላይ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የወረዳ ሁለት ንግድ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ወሊድ አንዋር ገልጸዋል።