ዜናዎች

የወረዳው ንግድ ጽ/ቤት የንግድ ሰርዓቱን ለማጠናከር የበር ለበር ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ላይ እንደሚገኝ አስታወቀ፡፡ ==============

አሶሳ ህዳር 26/2017ዓ.ም አሶሳ )
በአሶሳ ከተማ አስተዳደር የወረዳ ሁለት ንግድ ፅ/ቤት የንግድ ማህበረሰብ ህጋዊ በሆነ አግባብ የንግድ ስርአቱን ለማጠናከር በር ለበር ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ላይ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

በተደረገው የበር ለበር ክትትልና ቁጥጥር ተግባር ባልፀና የንግድ ፍቃድ ሲሰሩ ፣የአገልግሎት ጊዜያቸው ያለፈባቸው ምርቶችን ለሽያጭ የቀረቡ፣ የ2016 ዓ/ም ንግድ ፈቃድ ባለማደስ ሲነግዱ የተገኙ ንግድ ቤቶችን ላይ የማሸግ ስራ ተሰርቷል ።

በቀጣይ በወረዳ ደረጃ ህገወጥ የንግድ ተግባራትን ላይ የሚንቀሳቀሱ ነጋዴዎችን የግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ እየተሰራ በማይስተካከሉት ላይ የእርምት እርምጃ የመውሰድ ስራ በማጠናከር በሁሉም ቀበሌዎች ላይ የንግድ ህጋዊነትን ለማረጋገጥ እንሰራለን ሲሉ የፅ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ወሊድ አንዋር ተናግረዋል።

(የወረዳ ሁለት ንግድ እንዱስትሪ ትራንስፖርት ጽ/ቤት)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *