ዜናዎች

የንግድ ስራ ፈቃድዎን ያለቅጣት እንዲያሳድሱ ጥሪ ቀረበ፤ =============

(ታህሳስ 08/2017ዓ.ም አሶሳ)
የወረዳ ሁለት ንግድ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ወሊድ አንዋር በዛሬው ዕለት ባስተላለፉት መልዕክታቸው እንደገለጹት የ2017 በጀት ዓመት የንግድ ስራ ፈቃድ ያለቅጣት ማሳደሻ ጊዜ እየተጠናቀቀ በመሆኑ በወረዳችን የምትገኙ የበጀት ዓመቱን የንግድ ስራ ፈቃድ ያላሳደሳችሁ ነጋዴዎች ቀጠይ ባሉት በቀሪ ጊዜያት የንግድ ስራ ፈቃዳችሁን ከወድሁ ያለቅጣት እንድታሳድሱ ስሉ ጥሪ አቅርበዋል።

በንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር-980/2008 አንቀጽ 27 ንዑስ አንቀጽ 1 መሠረት አንድ ነጋዴ የንግድ ሥራ ፈቃዱን በበጀት ዓመቱ ከሐምሌ-01 እስካ ታህሳስ-30 ወይም ካስመዘገበዉ በጀት ዓመት መጨረሻ ጀምሮ ባሉት 6 ወራት ጊዜ ውስጥ ፈቃዱን ያለ ቅጣት ማሳደስ እንደሚቻል አዋጁ እንደምደነግግ ጭምር ኃላፊዉ አስገንዝበዋል።

አቶ ወሊድ አንዋር አክላውም በበጀት ዓመቱ የንግድ ስራ ፈቃዳቸውን በአዋጁ መሠረት በወቅቱ ያሳደሱ ነጋዴዎችን በመመስገን በወረዳችን የምገኙ ነገር ግን እስካ ዛሬ ድረስ ፈቃድ ያላሳደሳችሁ ነጋዴዎች የንግድ ስራ ፈቃድ ያለቅጣት ማሰደሻ ጊዜ ሊጠናቀቅ ከ(21)ቀናት ያነሰ ጊዜ የቀረ በመሆኑ የንግድ ስራ ፈቃዳችሁን ከወድሁ በማሳደስ በኃላ ሊደርስባችሁ ከሚችለው ከአላሰስፈላጊ ቅጣት እና እንግልት ራሳችሁን እንዲትጠብቁ በማለት አሳስበዋል።

በመጨረሻም በወረዳችን በየደረጀ የሚገኙ የንግድ መዋቅሮች በንግድ ተቋማቱ አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ በማድረግ የንግዱ ማህበረሰብ ባሉት በቀሪ ጊዜያት ፈቃዱን ያለቅጣት ማደስ እንዲችል የበርለበር ቅስቀሳ እና የማስገንዘብ ስራ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ኃላፊው ገልጸዋል።

\\\\ የንግድ ስራ ፈቃድዎን ያለቅጣት ያሳድሱ \\\\

\የወረዳ ሁለት ንግድ እንዱስትሪ ትራንስፖርት ጽ/ቤት\

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *